December 25, 2025
የአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ ዙር አምስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው። የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ፋንቱ ተስፋዬ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ በክልሉ እየታየ ያለው ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሒደት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡

እንደ ሀገርም ሆነ በክልሉ እየተመዘገበ ያለው ሁለንተናዊ የልማት እመርታ የዜጎችን ተስፋ በእጅጉ ያሳደገና ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ ነው ብለዋል፡፡ መንግሥት የጀመራቸውን ፕሮጀክቶች በውጤታማነት እንዲፈጽም ም/ቤቱ በሕዝብ የተጣለበት ኃላፊነት እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተዋል።
በቅርቡ በክልሉ መንግሥትና ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት ለክልሉ ሕዝብ የሰላም ፍላጎት በእጅጉ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ነው ያስታወሱት፡፡ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲወጣም አሳስበዋል። በጉባዔው የተለያዩ አዋጆች እና ሹመቶች ለምክር ቤቱ አባላት ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Source:
@NBC Ethiopia
Via:
NBC Ethiopia












