December 22, 2025
የሩሲያ ጀነራል በሞስኮ መገደላቸው ተነገረ፡፡ በመኪና ውስጥ በተጠመደ ቦምብ ጀነራሉ ህይወታቸውን ማጣታቸውን የአር ቲ ዘገባ ያሳያል፡፡

የሩሲያ የምርመራ ኮሚቴ ከፍተኛው ጀነራል ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከማረጋገጡም ባሻገር ምርመራውን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በደቡባዊ የከተማዋ ክፍል በርካታ ተሸከርካሪዎች ወድመዋል፤ አሽከርካሪውም ተጎድቷል፡፡
ሌተናንት ጀነራል ፋኒል ሳርቫሮቭ የኦፕሬሽናል ስልጠና መሪ እንደነበሩም ተነግሯል፡፡ የግድያው ሁኔታ ምንድን ነው የሚለውን የደህንነት ኃይሎች አሁንም በማጣራት ላይ ናቸው ተብሏል፡፡

የዩክሬን የኢንተለጀንስ አገልግሎት በጉዳዪ ላይ እጁ ሊኖርበት ይችላል የሚል ጥርጣሬም ሞስኮ አላት፡፡ ሳርቫሮቭ በመከላከያው ውስጥ ለከፍተኛ ባለሙያዎች ስልጠናን በማዘጋጀት እንዲሁም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ የሚታወቁ ነበሩ፡፡ ዘገባው የአር ቲ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBC Ethiopia












