December 16, 2025
6ኛው የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ስብሰባ የተካሄደ ሲሆን፣ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከል ኢትዮጵያ የትራንስፖረትና ሎጀስቲክ ዘርፏን በቴክኖሎጂ ማዘመን እንዲሁም አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎትን ማስፋፋት ላይ ያተኮሩት ይገኙበታል፡፡

ሚኒስትሩ ለምክር ቤት አባላት በሰጡት ምላሽ፤አማራጭ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማስፋት የኢትዮጵያ ዋና ጥረት ያለአግባብ ያጣችውን የባህር የማግኘት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የባለ ብዙ ወገን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት አዘጋጅነት ቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ በተካሄደው የባህር በር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ባተኮረው ጉባኤ፤ ወደብ አልበ ሀገራቱ ለችግሮች መጋለጣቸው አግባብነት የሌለው መሆኑ ከስምምነት የተደረሰበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በጉባኤው የተነሱ ስምምነቶችን ለመተግር እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በቀጣናው ያላትን ትስስር ለማጠናከር እና የሀገሪቷ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋጋጥ በሚሰሩ ስራዎች የመልቲ ሞዳል ኦፕሬተርን ወደ ሰባት ማሰደግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

እንዲሁም የጋራ ኮሪደርን ለመገንባት ከሀገራት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ነው የገጹት፡፡ የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስቴር የተሽከርካሪዎችን ሰሌዳ ዲጂታላይዝ በማድረግ ወደ ተግባር ለማውረድ እየሰራ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም የሰሌዳ ታርጋ እየተለዩ ለሚፈጸሙ ህገወጥ ድርጊቶች ለመቅረፍ እንደሚያግዙ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ አንስተዋል፡፡

በምክር ቤቱ በትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከተነሱ ችግሮች የተጀመሩ የአየር መንገዶችን የግንባታ አለመጠናቀቅ፣ ዲጂታል አገልግሎትን የማስፋት ብሎም በተለያዩ የሀገሪቷ ቦታዎች ህገ-ወጥ ኬላዎችን መበራከት ብሎም የትራፊክ አደጋ እና የቁጥጥር ስራዎች ክፍተት የተነሱ ጉዳዮች ናቸው፡፡
በ – ሰላም ይልማ












