NBC Ethiopia
December 9, 2025
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኑክሌር ኢነርጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ ዶ/ር ሜካኤል ቹዳኮቭ ጋር ተወያዩ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልእክትም፦
“ዛሬ ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኑክሌር ኢነርጂ ዲፓርትመንት ኃላፊ ዶ/ር ሜካኤል ቹዳኮቭ ጋር ትብብርን በሚያጠናክሩ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል።

ሀገራችን ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይልና ቴክኖሎጂን ለንጹህ ኢነርጂ፣ ለጤና፣ ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪና ለምርምር ልህቀት የመጠቀም ጽኑ መሻት ያላት ሲሆን፣ ለዚህም ሀገራዊ የኑክሌር ኃይል ፕሮግራምን በቅርቡ ጀምራለች፤ የኑክሌር ኃይል ኮሚሽንን በማቋቋምም በይፋ ወደ ሥራ ተገብቷል።

ኢትዮጵያ የኒውክሌር ኃይል ፕሮግራሟን ከዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ስታንዳርድና መመሪያዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ ትተገብራለች።
ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ሀገራችን ከኑክሌር ኃይል ስትራቴጂካዊ ተጠቀሚነቷን ለማረጋገጥ የጀመረችውን ጉዞ እውን ለማድረግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚያደርግ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀውልኛል፡፡” ብለዋል፡፡













