
በአማራ ክልል ደረጃ 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን የማጠቃለያ መርሀ ግብር በደብረብርሃን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
የማጠቃለያ መርሀ ግብሩ እየተካሄደ ያለው “ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።
በመርሃ ግብሩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ሰአዳ አብዱረህማን፣ የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አሲያ ከማል፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር እንዲሁም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












