
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ኮሚሽነር ጀነራሉ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የፖሊስ ለፖሊስ ግንኙነትን የበለጠ በማጠናከር ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ በልምድ ልውውጥ፣ በአቅም ግንባታ በትብብር አብሮ ለመስራት አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በበኩላቸው የሁለቱን ሀገራት ፖሊስ ለፖሊስ ግንኙትን የበለጠ ለማሳደግ ሀገራቸው ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልፀው በተለይም ሽብርተኝነትና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ እና በትብብር ለመከላከል አሜሪካ ቁርጠኛ መሆኗን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ አመላክቷል።
Source:
NBC Ethiopia
Via:
@NBCEthiopia












