Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

ኖርዌይ የኤርትራን መንግሥት ለሚደግፉ ትውልደ-ኤርትራውያን የሰጠችውን ዜግነት እንደምትነጥቅ አስታወቀች

ኖርዌይ የኤርትራን መንግሥት ለሚደግፉ ትውልደ-ኤርትራውያን የሰጠችውን ዜግነት እንደምትነጥቅ አስታወቀች

November 29, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

November 29, 2025

ኖርዌይ የኤርትራን መንግሥት የሚደግፉ ትውልደ ኤርትራውያንን ዜግነት እንደምትነጥቅ አስታወቀች።

የኖርዌይ የስደተኞች አገልግሎት ተቋም እንዳስታወቀው፤ ለሁለት ዓመታት ምርመራ ካደረገ በኋላ የኤርትራን መንግሥት የሚደግፉ ኖርዌጅያን-ኤርትራውያንን ዜግነት ለመንጠቅ ወስኗል።

የኖርዌይ ዜግነት የተሰጣቸው ኤርትራውያኑ ለኤርትራ መንግሥት ድጋፍ ይሰጣሉ ያለው አምስት አባላት ያሉት መርማሪ ኮሚቴ ነው። 135 ኤርትራውያን ላይ ምርመራ ያደረገ ሲሆን፤ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚጽፉትን እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለ እነሱ የሚናገሩትን ተከታትሏል። ምርመራ የተደረገባቸው 135 ሰዎች የኖርዌይ ዜግነት የተሰጣቸው ሲሆኑ፤ ላለፉት ስምንት ዓመታትም በአገሪቱ ኖረዋል። እስካሁን ድረስ 20 ሰዎች መኖሪያ ፈቃዳቸውን ሲነጠቁ፤ የሌሎች 30 ሰዎች ጉዳይ ደግሞ እየተመረመረ ነው።

በአጠቃላይ ምን ያህል ሰዎች ዜግነታቸውን እንደሚነጠቁ ግልጽ አይደለም። በኖርዌይ ሕግ መሠረት፤ በአገሪቱ ጥገኝነት የጠየቁ ሰዎች የሚሰጣቸው የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ዜግነት ሊነጠቅ ይችላል። የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ዜግነት የተሰጣቸው ስደተኞች አንዳች ስህተት ከተገኘባቸው ውሳኔው ሊቀለበስ እንደሚችል ሕጉ ይደረጋል።

የኖርዌይ መንግሥት የትውልደ ኤርትራውያንን የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ዜግነት ሲነጥቅ የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። ኤርትራውያን በትውልድ አገራቸው ሳሉ ለግዳጅ ውትድርና፣ ለእስራት፣ ለብዝበዛ እና ለስቅይት እንደሚጋለጡ በመጥቀስ በኖርዌይ ጥገኝነት ከጠየቁ በኋላ ለኤርትራ መንግሥት ድጋፍ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

የኖርዌይ የስደተኞች አገልግሎት ተቋም እንዳለው፤ ኤርትራውያኑ ለኖርዌይ መንግሥት የገለጿቸው የግዳጅ ብሔራዊ ውትድርና፣ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና እስራት ትክክለኛ አይደሉም። የኖርዌይ መንግሥት ምርመራ የከፈተው በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ከሁለት ዓመታት በፊት በተነሳው ግጭት ምክንያት ነው። በዚህ ግጭት ውስጥ ተሳታፊ ከነበሩ ኤርትራውያን አንዱ እአአ በ2013 በኖርዌይ ጥገኝነት ያገኘ ግለሰብ ነው።

የኖርዌይ የስደተኞች አገልግሎት ተቋም እንዳለው፤ ትውልደ ኤርትራውያኑ ላይ የተካሄደው ምርመራ በዋነኛነት ያተኮረው ለመንግሥት ድጋፍ በሚሰጡት ላይ ነው። በኦስሎ እና በርገን ከተሞች በመዘዋወር ምርመራውን ያካሄደ ሲሆን፤ በርገን ከዚህ ቀደም በኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች መካከል ግጭት የተከሰተባት ከተማ ናት። የኤርትራን መንግሥት የሚደግፉ ስደተኞች ላይ ምርመራ ከተከፈተ በኋላ ተቋርጦ የነበረ ሲሆን፤ በድጋሚ ምርመራው መጀመሩ ተገልጿል። ከአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት በኋላ የኤርትራውያኑ ይግባኝ እንደሚታይ የኖርዌይ የስደተኞች አገልግሎት ተቋም አስታውቋል።

በምርመራው ወቅት ስደተኞቹ ለምን የጥገኝት ጥያቄያቸው ተቀባይነት አገኘ? ለምን የሸሹትን መንግሥት ይደግፋሉ? የሚሉትም መፈተሻቸው ተገልጿል። መርማሪ ቡድኑ ከማኅበራዊ ሚዲያ ጽሑፎች በተጨማሪ ኖርዌይ ከሚኖሩ እና የኤርትራን መንግሥት ከሚቃወሙ ትውልደ ኤርትራውያን ጥቆማ ሰብስቧል። ለጥገኝነት ጥያቄ የተሳሳተ መረጃ ያቀረቡ ስደተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እና ዜግነትም ሊሰረዝ ይችላል። ወደ እስራኤል በሕገ ወጥ መልኩ የገባ እና የኤርትራ መንግሥትን በመደገፍ ይታወቃል የተባለ ኤርትራዊ ባለፈው ወር ወደ አገሩ መባረሩን የእስራአል መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸው ይታወሳል።

እስራኤል የኤርትራ ዜግነት ያለው እና የመንግሥት ደጋፊ የሆነን ግለሰብ ከአገሯ ስታባርር ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የአንድ ልጅ አባት የሆነው ኤርትራዊ ወደ እስራኤል የገባው በአውሮፓውያኑ 2011 ሲሆን፤ ላለፉት 14 ዓመታት ኑሮውን በዚያው አድርጎ ቆይቷል። እ.አ..አ በ2023 በእስራኤል መዲና ቴል አቪቭ በኤርትራውያን መካከል በተከሰተ ግጭት እስራኤላዊ ፖሊስን ጨምሮ 150 ሰዎች መጎዳታቸው ይታወሳል። የኤርትራ መንግሥት ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች ጎራ ለይተው በተሳተፉበት ግጭት 11 ሰዎች በጥይት ተመትዋል። እ.አ.አ በ2024 በነተሳ ግጭት ደግሞ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ ስምንት ሰዎች ክፉኛ መቁሰላቸው አይዘነጋም።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBC Ethiopia
Tags: #addisababaEritreaEthiopiaFacebookMetanorway
ShareTweetShare
Previous Post

ስታንዳርድ ባንክ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው

Next Post

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የአማራ ባንክ የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

የአማራ ባንክ የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ከደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ ከደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?