NBCEthiopia
የኢትዮ – ማሌዥያ የመጀመሪያው ቢዝነስ ፎረም ዛሬ አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በዝግጅቱ ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ባስተላለፉት መልእክት፣ የሁለቱን ሀገራት የጋራ እሴቶችና የልማት ምኞቶች አጉልተው አሳይተዋል፡፡
የማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያን ቀጠናዊ ሚና በማድነቅ ከመካ ወደ ኢትዮጵያ የተደረገውን ታሪካዊ የእስልምና እምነት ተከታዮችን ጉዞ (ሂጅራ) አስታውሰዋል።

በፎረሙ ላይ ማሌዥያ በማምረቻ፣ በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ፣ በቴክኖሎጂ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በመድሃኒት፣ በሎጂስቲክስና በኢነርጂ ዘርፎች ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ጥሪ ቀርቧል። ከፎረሙ አስከትሎም የፓናል ውይይት ውይይቶችን ተደርጓል።
በፎረሙ ላይ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዶ/ር ካሳሁን ጎፌ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በዝግጅቱ ላይ ተገኝተዋል።
የማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር ለሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ትላንት አዲስ አበባ መግባታቸው ይታወሳል፡፡ መረጃው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጽ/ቡቤት ነው፡፡













