በየዓመቱ ጥቅምት 17 በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተለያዩ አከባቢዎች በቦር ተራራ በመሰባሰብ መድኃኒት የሚለቅሙበት እንዲሁም በርካታ ጸጋዎችን ያቀፈ መሆኑ ይገለጻል።
20ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ምክንያት በማድረግ ምልከታ የሚያደርገውን የመገናኛ ብዙሃን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ተገኝቷል።

የየም ዞን አስተዳዳሪ ሽመልስ እጅጉ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተቀበሉ ሲሆን 20ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል በየም ብሔረሰብ ያሉትን ጸጋዎች ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል።
ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ስለ ቦር ተራራ ገለጻ ያደረጉት የየም ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ መስፍን ሞጋ ጥቅምት 17 በቦር ተራራ ላይ ባህላዊ መድኃኒት አዋቅዎች መድኃኒት ተለቅሞ የሚዘጋጅ መሆኑን ተናግረዋል።

የቦር ተራራ በየም ዞን ፎፋ ወረዳ የሚገኝ ሲሆን ከባህር ጠለል 2939 ሜትር ከፍታ እንዳለው ይነገራል።
ከ200 በላይ እጽዋትን ያቀፈ መሆኑ የሚገለጸው ስፍራው ሀገር በቀል እውቅት የሚንጸባረቅበት እና ለእንስሳትም ብሎም ለሰው ልጅ ፈውስ የሚሰጡ መድሀኒት የሚገኝበት ስለመሆኑ ተገልጿል።
20ኛው የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓል ምክንያት በማድረግ ምልከታ የሚያደርገውን የመገናኛ ብዙሃን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ተገኝቶ በርካታ ተፈጥሯዊና ሰውሰስራሽ ስፍራዎችን እየቃኘ ይገኛል።
በ-ሰላም ይልማ (ከየም ዞን)












