ሩሲያ “አሜሪካ የኑኩሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ክልከላ ስምምነትን እስካልጣሰች ድረስ በህጉ ተገዥ ነኝ”አለች። የክሬምሊን ቃል አቀባይ ድሚትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ በቅርቡ የሞከረቻቸው የጦር መሳሪያዎች” ኑክሌር ቀመስ” አለመሆናቸውን በማሳያነት አንስተዋል።
በሌላ በኩል ሩሲያ የኑክሌር አቅም ያለው ሚሳዔል አስወንጭፋለች በሚል በስጋት መልክ የሚያነሱባት ተበራክተዋል። በሌላ በኩል ሞስኮ የኑክሌር ሙከራ ክልከላ ዓለም አቀፍ አሰራርን እንደማትጥስ አሳውቃለች።
ሌሎች አገራት የሚሞክሩ ከሆነ ግን እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም ብለዋል ፔስኮቭ። ዋይት ሀውስ ስምምነቱን ካልጣሰ ክሬምሊን ምንም ዓይነት የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ እያደርግም ብለዋል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቤይጂንግና ሞስኮ በምስጢር የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ አድርገዋል በሚልም ይወቅሳሉ። በእርግጥ ቻይናም ሆነች ሩሲያ የትራምፕን ውንጀላ ከእውነታው ያፈነገጠ በሚል በተደጋጋሚ ውድቅ አድርገውታል።
አር ቲ እንዳስነበበው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












