እየመጣ ባለው ፈታኝ የቅዝቃዜ ወራት ፍልስጤማውያን አሁንም በቂ የሰብአዊ እርዳታን ሳያገኙ ለከፉ ችግር እየተጋለጡ መሆኑ ተሰምቷል። ሀማስ በበኩሉ በአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ቡድን በኩል የእስራኤል አካላትን በመመለስ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል ።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ቢሮ , አካላቱን ከሀማስ ስለመቀበሉ አረጋግጧል፤ ሆኖም አሁንም ቀሪ ስድስት አካላት(ህይወታቸው ያለፈ እስራኤላውያን አካሎች) ይቀራሉም ተብሏል።
በአሜሪካ በቀረበው የሰላም ስምምነት መሰረት የእስራኤል ታጋቾችን እና አስክሬኖችን የመመለስ ስራ ቀዳሚው የነበረ ቢሆንም፤ ሀማስ ስምምነቱን ሳያከብር ቀርቷል ስትል እስራኤል ትከሳለች። ሀማስ በበኩሉ አካላቱን ሙሉ ለሙሉ መልሶ ለመጨረስ ከተቀበሩበት የማፈላለግ ሁኔታ ፈታኝ በመሆኑ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ሲጠይቅ ቆይቷል።
በመጀመሪያው ዙር ስምምነት መሰረት የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገቡ የተዘጉ መስመሮችን የመክፈት የእስራኤል የሚጠበቅ ነበር፤ ሆኖም የሀማስ ታጋቾችን በተገቢው አለመልቀቅ በሚል የሰብአዊ እርዳታ በተገቢው መልኩ እንዳይገባ ሆኗል ተብሏል።
ቴላቪቭ ታጋቾቼን ሙሉ ለሙሉ ሳልቀበል የሰብአዊ እርዳታ የማይታሰብ ነው ስትል ቆይታለች፤ ይህም በጋዛ ያለው ሰብአዊ ቀውስ እንዲቀጥል ስለማድረጉ ይገለፃል።
አልጀዚራ ዘግቦታል
በ-የአብስራ ሚሊዮን












