የባርሴሎናው ሳግራዳ ፋሚልያ ባሲሊካ የዋናው ማማው አንድ ክፍል ወደ ስፍራው መግባቱን ተከትሎ ሐሙስ ዕለት የአለማችን ረጅሙ ቤተክርስቲያን ሆኗል።
ቤተክርስቲያኑ በሰጠው መግለጫ መሠረት፣ የአርክቴክት አንቶኒ ጋውዲ ታላቁ ስራ የሆነው ይኸው ቤተክርስቲያን አሁን ከከተማዋ በላይ 162.91 ሜትር ከፍታ አለው።
ከአሁን በፊት በ1543 እና በ1890 መካከል በጀርመን የተገነባው የጎቲክ ሉተራን ቤተክርስቲያን የሆነው ኡልመር ሙንስተር የአለማችን ረጅሙ ቤተክርስቲያን የሚለውን ማዕረግ ይዞ ቆይቷል። ይሁንና ያ ማዕረግ አሁን ወደ ስፔናዊው ተቀናቃኙ አልፏል።
ሳግራዳ ፋሚሊያ ሪከርዱን የሰበረው እስካሁን የሪከርዱ ባለቤት የነበረውን የጀርመኑን ኡልመር ሙንስተርን ከፍታ በ1.4 ሜትር በመብለጥ ነው።
ሳግራዳ ፋሚልያ አሁንም ግንባታው ያልተጠናቀ ሲሆን ከቤተክርስቲያኑ አናት ላይ እየተገነባ ያለው ማዕከላዊው “የኢየሱስ ክርስቶስ ማማ” በቀጣይ ወራት ሲጠናቀቅ 172 ሜትር ከፍታ ይኖረዋል።
በ-ዳንኤል መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












