ዓለም አቀፉ የኅዋ ጣቢያ (International Space Station) በዚህ ሳምንት መጨረሻ የሩብ ምዕተ ዓመት ያህል ቀጣይነት ያለው የሰዎች ቆይታ እያከበረ ነው።
ላለፉት 25 ዓመታት ሰዎች ከፕላኔቷ ውጪ በምህዋር ላይ ያልነበሩበት ቅጽበት አልነበረም። ይህም በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ የኅዋ ላይ ስኬት ነው ተብሎለታል።
የጎብኚዎቹ ዝርዝር ወደ 300 የሚጠጉ ሰዎችን ያስመዘገበ ሲሆን — አብዛኛዎቹ ሙያዊ የኅዋ ተጓዦች (astronauts) ሲሆኑ አልፎ አልፎም የሚመጡ የኅዋ ቱሪስቶች እና የፊልም ዳይሬክተሮችን ያካትታል። የመጀመሪያዎቹ ቋሚ ነዋሪዎች የጣቢያውን በር የከፈቱት እ.ኤ.አ ህዳር 2፣ 2000 ዓ.ም. ነበር።
ይህ ሳይንሳዊ ጣቢያ ከዚህ በኋላ አገልግሎት የሚሰጠው ለአምስት ዓመታት ብቻ ሲሆን ከዚያ በኋላ የግል ኩባንያዎች የራሳቸውን የምሕዋር ጣቢያዎች የበለጠ እና ሰፋ ባለ የደንበኞች ስብስብ እንደሚያስጀምሩ ያለውን እምነት ናሳ (NASA) ገልጿል።
በ- ዳንኤል መኮንን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












