የሜክሲኮዋ ፕሬዚዳንት አሜሪካ በካርቢያን ባህር እና ፓስፊክ ውቅያኖስ የምትፈጽመውን ጥቃት አወገዙ።
ፕሬዚዳንት ክላውዲያ ሼይንባውም ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፍተኛ የድንበር ላይ ጫና እየተፈጠረባቸው ይገኛል። በድንበር አካባቢ ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ውጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል ሪፐብሊካኑ ሼይንባውምን ይወነጅላሉ።
በሌላ በኩል በአሁኑ ሰዓት ‘አሜሪካ ከአደንዛዥ ዕጽ ጋር ትሥሥር አላቸው ያለቻቸውን መርከቦች ዒላማ ውስጥ ማስገበቷን ደግሞ ፕሬዚዳንቷ ”አንቀበለውም ፣በዚህ አንስማማም” ብለዋል። ከነሐሴ መጨረሻ አንስቶ የአሜሪካ ኃይሎች በካርቢያን ባህር እንዲሁም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በፓስፊክ ውቅያኖስ ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው።
ምንም እንዃን ፔንታጎን ህገ ወጥ መርከቦች ናቸው በማለት ቢያስተባብልም ድርጊቱ ዓለም አቀፍ ህግን የሚጥስ ነው በሚል ይተቻል።
በዓለም አቀፍ ባህር ላይ እንዴት ህገ ወጥ የአደንዛዥ ዕጽ አዘዋዋሪዎችን መግታት እንደሚቻል አሰራር አለ የሚሉት ሼይንባውም ቢያንስ የ37 ሰዎችን ህይወት የቀማውን የአሜሪካ ተከታታይ ጥቃት አውግዘዋል።
በአሜሪካ-ሜክሲኮ ድንበር ፍልሰተኞችን በመቆጣጠርና በንግድ እሰጥ አገባ ውስጥ ያሉት ዋሽንግተንና ሜክሲኮ አሁን ላይ ደግሞ የካሪቢያን ባህር ቀውስ ውስጥ እንዳይገቡም ተሰግቷል ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












