ጆሽኮ ግቫርዲዮል በታዳጊነቱ እግር ኳስን አቁሞ ወደ ቅርጫት ኳስ ሊጀምር እንደነብር ተናገረ።
የማንችስተር ሲቲው ተከላካይ ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ በሃገሩ ክለብ ዳይናሞ ዛግሬብ በ16 አመቱ በቂ የመሰለፍ ዕድል ባለማግኘቱ እግር ኳስን ሊያቆም እንደነበር ገልጿል። የ23 አመቱ ተከላካይ “ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች የመሆን ፍላጎት የነበረኝ ቢሆንም፤ ያን ጊዜ በቂ እድል አለማግኘቴ ወደ ቅርጫት ኳስ ስፖርት እንድሄድ ይገፋፋኝ ነበር” ብሏል።
ግቫርዲዮል ጠንክሮ በመስራቱ እና በዋናው ቡድን የመሰለፍ ዕድል ሲያገኝ ባሳየው አቋም ከክሮሺያው ሃያል ቡድን ዳይናሞ ዛግሬብ በተከታታይ አመት የሊግ አሸነፊ በመሆን፤ በሃገሪቱ ሊግ ከፍተኛ በተባለው የ16 ሚሊዮን ዩሮ የዝውውር ሂሳብ ወደ ጀርመኑ አርቢ ላይብዚሽ ሊዘዋወር ችሏል።
ተጫዋቹ በ2023 ከአርቢ ላይብዚሽ ወደ ማንችስተር ሲቲ በ77 ሚሊዮን ዩሮ ሲያቀና፤ በአለማችን በከፍተኛ የዝውውር ሂሳብ የተዘዋወረ ሁለተኛው ተከላካይ አድርጎታል። በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ቡድን ቁልፍ ከሚባሉ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው ግቫርዲዮል፤ ግብ በማስቆጠር ከሚጠቀሱ ተከላካዮች ዋነኛው ሆኗል።
ግቫርዲዮል ከአምስት አመት በፊት ብትጠይቁኝ አሁን ባለሁበት ደረጃ እገኛለሁ የሚል ተስፋ ጨርሶ አልነበረኝም ሲል፤ ራሱን ከዚህም በላይ ለማሳደግ እንደሚተጋ ገልጿል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












