የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ ”የጋዛው ተኩስ አቁም በጥሩ ሂደት ላይ ነው ያለው” አሉ።
ምንም እንኳን ተኩስ አቁሙ በተለያዩ ምክንያቶች ገቢራዊ አለመሆኑን የሚያሳዩ ክስተቶች ቢኖሩም ቫንስ ተስፋቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው። አንዳንድ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ እየቀጠሉ ላይሆን እንደሚችል ያስታወሱት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ገላጋይ መሆን እና ቁጥጥር ማድረግ መልካም ውጤት ይዞ ይመጣል በሚል አረጋግጠዋል።
በአሁኑ ሰዓት ጥሩ ነገር ይሰማኛልም ብለዋል ጄዲ ቫንስ። ሃማስ የታጋች አስክሬንን ለመመለስም ቢሆን በአንድ ምሽት የሚያደርገው አይደለም በሚል ሀሳባቸውን አጋርተዋል። ብዙ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው የጠቆሙት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ ዶናልድ ትራምፕ መፍትሄ እንደሚያመጡ አምናለሁ ሲሉም ተደምጠዋል።
በእስራኤል ጉብኝት የማድረጋቸው ምስጢርም በጋዛ የተደረሰውን ተኩስ አቁም ለማጠናከር ነው ተብሏል። ከእስራኤል ፖለቲከኞች ጋርም ምክክር አድርገዋል የትራምፕ የመካለለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ቫንስ።
ዘገባው የቢ ቢ ሲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












