የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬም ሲቀጥሉ ሪያል ማድሪድ ከ ጁቬንቱስ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
የቻምፒዮንስ ሊግ 3ኛ ዙር ቀሪ ጨዋታ በሳንቲያጎ ቤርናባው ሪያል ማድሪድን ከጁቬንቱስ አገናኝቷል። ሁለቱ ቡድኖች በአለም የክለቦች ዋንጫ ተገናኝተው ማድሪድ 1-0 ማሸመፉ ይታወሳል። በዚሁ መድረክ ሲገናኙ ከአመታት በኋላ ሲሆን፤ ማድሪድ ከፍተኛ የውጤት የበላይነትን ይዟል።
ሁለቱ ቡድኖች ካደረጓቸው ያለፉት ሁለት የቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች ማድሪድ ኬራት አልማቲ እና ኦሎምፒክ ማርሴይን ሲያሸንፍ፣ ጁቬንቱስ ከቪላሪያል እና ቦሩሲያ ዶርትሞንድ አቻ ተለያይቷል።
ምሽት 4 ሰዓት በሚደረገው ጨዋታ ሎስ ብላንኮዎቹ እንደ ዲን ሃውሰን፣ ዳኒ ካርቫሃል እና ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ ያሉ ወሳኝ ተጫዋቾችን በጉዳት ሲያጣ፤ በተመሳሳይ ዩቬ ብሬመን እና ካባልን ከቡድን ስብስብ ውጪ አድርጓቸዋል።
በተመሳሳይ ምሽት 4 ሰዓት ከ4 ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት ለማገገም ሊቨርፑል ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ኢንትራክት ፍራንክፈርትን ሲገጥም፣ ቼልሲ ከአያክስ፣ ሞናኮ ከቶተንሃም፣ ባየር ሙኒክ ከክለብ ብራግ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












