መድረኩ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማረጋገጥ በትራንስፖርት ዘርፉ ታዳሽ ኃይልን እንዲጠቀም ለማስቻል ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር ) ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለማስፋፋት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆነን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የትራንስፖርት ዘርፉ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪ ቁጥርን ለማሳደግ እየሰራች መሆኑ በማንሳት አሁን ላይ አንድ መቶ ሺህ የተሻገሩ የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎችን መኖራቸውን አንስተዋል። በ2030 ደግሞ 500 ሺህ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎች በኤሌትሪክ የሚሰሩ ለማድረግ ውጥን መያዙ ነው የገለጹት።
በነዳጅ የሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎችን መጠቅም ኢትዮጵያ በዓመት ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስወጣ የተመላከት ሲሆን በትራንስፖርት ዘርፉ ታዳሽ ኃይልን መጠቀም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።
የአፍሪካ ኢ ሞቢሊቲ ሳምንት ጉባኤ የአፍሪካ ሀገራት የአየር ንብረት ለመከላከል በትራንስፖርት ዘርፉ ታዳሽ ኃይል ለመጠቀም፤በዘርፉ ላይ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እና የአህጉሪቱን መጻኢ ዕድል ለመወሰን የሚያግዙ ሀሳቦች የሚቀርብበት መሆኑ ተነስቷል።
ዛሬን ጨምሮ ለ3 ቀናት በሚቆየው የአፍሪካ ኢ ሞቢሊቲ ሳምንት ጉባኤ ፖሊሲ አውጪዎች፣ኢንቨስተሮች፣ ኢንተርፕራይዞች እና በዘርፉ ላይ የሚሰሩ አካላት የታደሙበት ነው።
በ-ሰላም ይልማ












