ሬንጀርስ ስቴቨን ጄራርድን በድጋሚ በአሰልጣኝነት ለመቅጠር ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተዘገበ።
የስኮትላንዱ ክለብ ሬንጀርስ ከቀናት በፊት አሰልጣኝ ረስል ማርቲንን በውጤት መጥፋት ሳቢያ እንዳሰናበተ ይታወሳል። ክለቡ አሁን ላይ የተለያዩ አሰልጣኞችን ለመተካት እጩዎችን መያዙን የዘገበው ስካይ ስፖርት ዋነኛው ፍላጎታቸው ስቴቨን ጄራርድን በድጋሚ በሃላፊነት መቅጠር መሆኑን ጠቁሟል።
የቀድሞው የሊቨርፑል ታሪካዊ ተጫዋች ጄራርድ በ2021 ሬንጀርስን በማሰልጠን የስኮትላንድ ሊግን ሻምፒዮን ማድረጉ አይዘነጋም። አሰልጣኙ ከዚያም ወዲህ አስቶን ቪላን ካሰለጠነ በኋላ ወደ ሳኡዲ ሊግ በማቅናት እስካሳለፍነው የውድድር አመት አጋማሽ በስራ ላይ ቆይቷል።
ጄራርድ አሁን ላይ በማንኛውም የማሰልጠን ስራ ላይ የማይገኝ ሲሆን፤ በባህሬን ከቤተሰቡ ጋር እንደሚገኝ ዘገባው አመላክቷል። ሬንጀርስ በቀጣዮቹ ቀናት በግል ጉዳዮች ላይ ያነጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
የ45 አመቱ እንግሊዛዊ ወደ ስኮንትላድ ሊግ በድጋሚ የመመለስ ፍላጎቱን በተመለከት ግን የተባለ ነገር የለም።
በ-አልፈሪድ ነስሮ












