የፍልስጤሙ ሃማስ እስራኤል ከጋዛ ጠቅልላ እንድትወጣ እንዲሁም ዋስትና እንዲሰጠው ይፈልጋል ተባለ።
ሃማስ ተይዘው የሚገኙ እስራኤላውያንን የመልቀቅ ፍላጎት እንዳለውም የተነገረ ሲሆን ያም ሆኖ ግን አይ ዲ ኤፍ ከጋዛ መውጣት እንዳለበት ሀሳብ ሰቷል። ሁለተኛው ቀን ድርድር በግብጽ እንደተጠናቀቀ ሃማስ ሀሳቡን ለአልጀዚራ ሰቷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያቀረቡት የ20 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ገቢራዊ መደረግ ካልቻለ አሁንም ውጥረቱ ተባብሶ ሊቀጥል ይችላል። ጦርነቱ የተቀሰቀሰበትን 2ኛ ዓመት አስመልክቶ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተያየት ሲሰጡ የጋዛውን ጦርነት ለመቋጨት ተጨባጭ ዕድል አለ ብለዋል።
በሻርም ኤል- ሼይክ ግብጽ እየተደረገ ያለው ድርድር መፍትሄ ሊያመጣ እንደሚችልም ተስፋ ተጥሎበታል። የኳታርና የአሜሪካ ተወካዮችም ከእስራኤልና ሃማስ ሰዎች ኢ-ቀጥተኛ ድርድር በተጨማሪ ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት ወደ ግብጽ ማቅናታቸው ይታወሳል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












