ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ አል ኢቲሃድን ለማሰልጠን ተስማሙ።
ባሳለፍነው የውድድር አመት ኤሲ ሚላንን ያሰለጠኑት ሰርጂዮ ኮንሴሳኦ ወደ ሳኡዲ አረቢያ ሊግ አቅንተው አል ኢቲሃድን ለማሰልጠን ከስምምነት ደርሰዋል። ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ የአምናውን የሳኡዲ ሊግ አሸናፊ እስከ አውሮፓውያኑ 2027 ድረስ ለማሰልጠን ፊርማቸውን አኑረዋል።
አሰልጣኝ ኮንሴሳኦ የአሰልጣኝ ቡድን አባላቶታቸውን በሙሉ ይዘው የተጓዙ ሲሆን፤ ከፍ ያለ ውጤታማነት እንዲያሳዩ ተጠብቆባቸዋል። ኮንሴሳኦ አል ኢቲሃድን የተረከቡት ክለቡ አሰልጣኝ ሎረን ብሎን በሳኡዲ ፕሮ ሊግ በአልናስር ከተሸነፉ ወዲህ መሆኑ ነው።
እየተካሄደ በሚገኘው እና 4ኛ ሳምንት በደረሰው የሳኡዲ ፕሮ ሊግ ካሪም ቤንዜማ እና ንጎሎ ካንቴን የመሳሰሉ ኮከቦች የያዘው አል ኢቲሃድ 9 ነጥብ ይዞ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












