የአሜሪካ መንግስት መዘጋትን ተከትሎ ግዙፍ የአገሪቱ አውሮፕላን ማረፊያዎች ተጓዦችን ማስተናገድ ተሳናቸው።
ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የመንግስት መዘጋት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎችን በቤታቸው እንዲቀመጡ አድርጓል። በቺካጎው ኦ’ሄር ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያም በቂ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንደማይኖሩ ተወስቷል።
የፌደራል አቪዬሺን አስተዳደሩም ማስጠንቀቂያ በመስጠት ላይ ይገኛል። በናሽቪል እጅግ በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰራተኞች ቤታቸው ውስጥ እንዲቀመጡ በመገደዳቸው አውሮፕላኖች ከአየር ማረፊያው እንዲወጡና እንዲገቡ የሚያደርገው የመቆጣጠሪያ መሳሪያ ሳይቀር አገልግሎት እየሰጠ አይደለም።
በመላ አገሪቱ ያለው የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር(FAA) ቢሮዎችም ተመሳሳይ ዕጣ ደርሷቸዋል። የመንግስት መስሪያ ቤቶች መዘጋት በአየር መንገዶች ላይ የሚታይ ቀውስ ማምጣቱንም የቀጠለ ሲሆን ለተፈጠረው የዴሞክራቶችና ሪፐብሊካኖች ልዩነት መፍትሄ ካልመጣ አደጋም ሊከሰትም ይችላል ተብሏል።
በሂዩስተን፣ ኒዋርክ(ኒውጀርሲ) እና ላስ ቬጋስ የቁጥጥር ስራውን የሚከውን ባለሙያ እንደሌለም በተመሳሳይ ተነግሯል። የአሜሪካ ኮንግረስ የበጀት ጉዳዩን መርምሮ የመንግስትን ስራ ማስጀመር ካልቻለ ከአቪዬሺን ዘርፉ በተጨማሪ ሌሎች ዘርፎችም ይጎዳሉ ተብሏል።
ዘገባው የ ሲ ኤን ኤን ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












