የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኖቤል የሰላም ሽልማት እኔን መከልከል አሜሪካንን እንደመስደብ,እንደመናቅ ነው አሉ።
ዶናልድ ትራምፕ በቨርጂኒያ ኳንቲኮ የሀገሪቱን ከፍተኛ የጦር ጀነራሎች ባነጋገሩበት ወቅት ነው በኖቤል ላይ ያላቸውን ቅሬታ ያነሱት፤ ምንም እንኳ ለኖቤል ሽልማት አስፈላጊውን መስፈርት ቢያሟሉም በተደጋጋሚ ችላ መባላቸውን አስረድተዋል።
ትራምፕ ኖቤል ለምን እንደሚገባቸው ሲያስረዱም ዳግም ወደ ስልጣነ መንበሩ ከመጡ እንኳን የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ጨምሮ ስምንት ጦርነቶችን ማስቆማቸውን ተናግረዋል። ኖቤል ሽልማት በተቃራኒው ምንም አበርክቶ ለሌላቸውና , ለደራሲያን ይሸልማል፤ በርግጥ ሽልማቱን ለእኔ ሳይሆን ለሀገሬ እንዲሆን ነው የምፈልገው ሲሉ ትራምፕ አስረድተዋል።
ትራምፕ ጦርነት አስቁሜያለሁ ካሉት ሀገራት መካከል ኮንጎና ሩዋንዳ ፣ አርሜኒያ እና አዘርባጃን፣ እስራኤል እና ኢራንና ሌሎችም አንስተዋል።
ዘገባው የአርቲ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












