የእስራኤል የባህር ሀይሎች እርዳታ ጭነው ወደ ጋዛ ሲያቀኑ የነበሩ ጀልባዎችን ማስቆማቸውን አስታውቀዋል።
የባህር ሀይሎቹ ከ500 በላይ ሰዎችን እና የእርዳታ ቁሳቁሶችን የጫኑ ከ40 በላይ ጀልባዎችን ማስቆማቸውን ተናግረዋል። ጀልባዎቹ ወደ ጋዛ ምድር ለመግባት የ75 ማይል ርቀት ላይ ነበሩ ተብሏል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋች ስዊዲናዊቷ ግሬታ ተምበርግ ጨምሮ ሌሎች አክቲቪስቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉንና በደህንነት ላይ እንዳሉ አስታውቋል። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጋዛ እርዳታን የሚያሰባስብ አለም አቀፉ የእርዳታ ቡድን (ጂ. ኤስ. ኤፍ) አካል የሆኑ በርካታ ጀልባዎች በአስተማማኝ ሁኔታ አቁመናል ያለ ሲሆን፤ በጀልባዎቹ የነበሩ ሰዎችና የሰብአዊ እርዳታ ቁሳቁሶች ወደ እስራኤል ወደብ እየተዘዋወሩ እንደሚገኙ አስታውቋል።
እስራኤል በሰብአዊ እርዳታን በሚያከፉፍሉ ቡድኖች ላይ መሰል ድርጊት መፈፀሟን አለምአቀፍ ተቋማት እያወገዙ ይገኛሉ።
ዘገባው የቢቢሲ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












