የመስቀል በአል እየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ፍቅር በመስቀል ያሳየበት በማሰብ የሚከበር ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ። የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በአል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ክዋኔዎች በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ይገኛል።
በስፍራው የተገኙት የአዲስ አበባ ከንቲባ የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በአል በህዝቦች የተባበረ ክንድ እውን የሆነው የታላቁ የኢትዮጵየሰ ህዳሴ መጠናቀቁን ማግስት የሚከበር መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን እድገት ለማረጋገጥ እንደደመራው በመደመር፣ በመስቀሉን ፍለጋ የታየውን አንድነት ምሳሌ በማድረግ የተጀመረው የእድገት ጎዳና ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።
ለመስቀል ደመራ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ኢትዮጵያ የብዝሃን ማንነት ያላት ሀገር መሆኗን ከሚያሳዩት መስቀል በአል አንዱ መሆኑን አንስተዋል።
በአብዛኛው የሀገሪቷ አከባቢዎች የሚከበር በዓሉ በተለያየ ሁነት የሚከበር ነው ይህም አንድነታችንን የሚያሳይ ነው ብለዋል። ዛሬ የምናከብረው የመስቀል ደመራ በዓል የብዙዎች ጥረት የተደረገበት ነው ያሉ ሲሆንየሀገራችንን እድገት ለማስቀጠለም የጋራ ጥረት ያስገልጋል ነው ያሉት የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ።
አብሮነት ማሳያ የሆነው በዓሉ ትውፊቱን በሚመጥን መልኩ ለማስቀጠል ሁላችንም ኃላፊነት አለብን ብለዋል። የዘንድሮ መስቀል ኢትዮጵያ በርካታ ፈተና አልፋ በማንሰራራት ጎዳና ላይ ሆና ማክበሯ የተለየ ያደርገዋል ሲሉም ሸዊት ሻንካ ተናግረዋል።
በዓሉ የፍቅር፣ የመረዳዳትና አንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።












