በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የመስቀል ደመራ በዓል በድምቀት እየተከበረ ነው።
በዓሉ እየተከበረ ያለው በባህር ዳር፣ በደሴ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደብረ ማርቆስ፣ በወልዲያና በሌሎች የክልሉ ከተሞች እንዲሁም በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች መሆኑ ተመላክቷል።
በየአካባቢው በዓሉ እየተከበረ ያለው በርካታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሃይማኖት ተከታዮች፣ የእምነቱ አባቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት እየተከበረ ነው።
በደመራ በዓል ማክበሪያ ስፍራዎች ወረብ ከቀረበና ለምዕመናን ትምህርት ከተሰጠ በኋላ በጋራ ደመራ የመለኮስ ሥነ ስርአት ማምሻውን ይከናወናል።
በጎንደር፣ በላልይበላ፣ በሰቆጣና በሌሎች የሰሜኑ አካባቢ በሚገኙ ከተሞችም የመስቀል ደመራውን ዛሬ ምሽት በመደመር በነገው እለት ጧት ረፋድ ላይ የሚለኮስ ሥነ ስርዓት እንደሚከናወን ታውቋል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












