የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዎስቆሮስ እንዲሁም የአ/አ አገረ ስብከት ሊቀ ዻዻስ ብፁዕ አቡነ ህርያቆስ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጋር የመስቀል ደመራ በዓል ቅድመ ዝግጅት እና በከተማዉ አስተዳደር ስለሚደረገዉ ድጋፍ ዙሪያ ተወያይተዋል።
የመስቀል ደመራ በዓል መስቀል አደባባይን ጨምሮ በ 2375 ደብሮችና ቦታዎች ላይ የሚከበር መሆኑ በመጥቀስ ሃይማኖታዊ ቱፊቱን እና ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀና ባማረ መልኩ እንዲከበር የከተማዉ አስተዳደር ከማእከል እስከ ወረዳ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን በመግለፅ አባቶች እና የኮሚቴዉ አባላት እየተደረገ ላለዉ ድጋፍ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዉይይቱ የበዓሉ ዋና ባለቤትና በአሉን የምትመራዉ፣ የምታስተባብረዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡
የመስቀል ደመራ በዓል ከፍተኛ ቁጥር ያለዉ ህዝብ በአደባባይ የሚያከብረዉ የአገር ሀብት ፣የከተማችን ድምቀት ፣ የቱሪዝም መስህብ ነዉ ያሉ ሲሆን ሃይማኖታዊ ቱፊቱን እና እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እንዲከበር፣ አብሮትን በሚያጠናክር መልኩ እና በሰላም እንዲጠናቀቅ ለሌሎችም የአደባባይ ክብረ በአላት የሚያደርገዉን ድጋፍ የከተማዉ አስተዳደር ይቀጥላል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት












