ዴንማርክ በውል ያልተለዩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች(ድሮንስ) በኮፐንሀገን አየር ማረፊያ ላይ በመታየታቸው አገልግሎቷን ዘጋች።
ቢያንስ 15 በረራዎች ችግሩ እስከሚቀረፍ ድረስ አቅጣጫቸውን እንዲቀይሩ ተደርገዋል። ከሁለት እስከ ሶስት የሚሆኑ ድሮኖች በአየር ማረፊያው ላይ በመታየታቸው አየር መንገዱ ተዝግቷል ብለዋል የተቋሙ ቃል አቀባይ።
ምንም ዓይነት በረራ ከኮፐንሀገንም ወደ ኮፐንሀገንም እየተደረገ እንዳልሆነ ጠቁመዋል ቃል አቀባይዋ። በአየር ማረፊያው ላይ ከሶስት እስከ አራት የሚደርሱ ሰው አልባ አውሮፕላኖች መታየታቸውን ደግሞ ፖሊስ አረጋግጧል።

ድሮኖቹ በጣቢያው ላይ በመመላለስ ላይ መሆናቸውን ያሳወቀው የኮፐንሀገን ፖሊስ ምን እንደሆኑ ለመለየት ምርመራ ላይ ነኝ ብሏል። ድሮኖቹ ወታደራዊ ይሁኑ ለሌላ ዓላማ የሚውሉ በግልጽ አልተለዩም።
ግለሰቦች ከሚይዟቸው ድሮኖች በመጠን ከፍ ያሉ መሆናቸውን ግን የኮፐንሀገን ፖሊስ ይፋ አድርጓል። እንዲህ ዓይነቱ ሀሳብ የመጣው ሶስት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ጥምረት ዓባላት የአየር ክልላችን በሩሲያ ተጥሷል ባሉበት አጋጠሚ ነው።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












