የባማኮን ኢንጂነሪንግ እህት ኩባንያ የሆነው ባማኮን ሪል እስቴት በካዛንቺስ ያስገነባውን ጋላክሲ የፊኒሺግ ሞል አስመርቋል።
በከፍተኛ ጥራት ዲዛይን ተሠርቶ የተጠናቀቀው ጋላክሲ ፊንሽንግ ሞል የኪነ ሕንጻ ባለሙያዎች፣ ሻጭ እና ገዥዎችን እንዲሁም አቅራቢዎችንና ሌሎች በአንድ ጣሪያ ስር በማሰባሰብ ወጪን የሚቆጥብ መሆን ተመላክቷል።
ጋላክሲ ፊኒሺንግ ሞል የግንባታ መሠረት ከማስቀመጥ እስከ ፊኒሺንግ ሥራ ድረስ በድርጅቱ ሙሉ አቅም የተሠራ መሆኑን ተገልጿል። ሪል እስቴቱ በከተማ አስተዳደሩ እየተገነቡ ያሉ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ ማድረጊያዎችን ማሟላቱ ተጠቁሟል።
በ-አማኑኤል ምትኩ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












