በኢትዮጵያ የአየር ጠባይ መረጃ ትንበያ እና የትንተና ሥርዓት በማዘመን አደጋዎችን መቀነስ ተችሏል ሲሉ የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ተናገሩ።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሀገሪቱ የአየር ጠባይ ሁኔታን ትንበያ ሥርዓትን ለማዘመን በተሰሩ ስራዎች የሚከሰቱ የጎርፍ አደጋን ጨምሮ መቀነስ መቻሉን ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት። የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የባለፈው የክረምት ወቅት ትንበያ ግምገማ እና የመጪው በጋ ወቅት ትንበያ ይፋ የሚያደርግበት መድረክ እየተካሄደ ነው።
በመረጃ የተደገፈ የትንበያ ሥርዓት በመዘርጋት በየጊዜው መረጃዎችን በመተንተን ብሎም ለማህበረሰቡ በማድረስ ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን መቀነስ መቻሉ ነው የተገለጸው።
የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ዘመናዊ የሚቲዎሮሎጂ ጣቢያዎችን እያስፋፋ እንደሚገኝና የሚሰጠውን የአየር ጠባይ መረጃ ብሎም የሚጠቀመው የህብረተሰብ ቁጥርም እየጨመረ መምጣቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል ።
በ – ሰላማዊት ወልደገሪማ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












