የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ቀደማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ከመሃል ለንደን ዊንፊልድ ሀውስ ተነስተው ዊንድሰር ካስትል ደረሱ፡፡
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ኪንግደም የክብር አቀባበል ተድርጎላቸዋል፡፡ የዌልስ ልዑልና ልዕልትም በዊንደሰር ካስትል ደማቁን አቀባበል ሲያደርጉላቸው በአደባባይ ተመልክቷል፡፡
ለራሳቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕም ታሪካዊ አጋጣሚን የፈጠረ ጉዞ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ አሜሪካ ወሳኝ የብሪታንያ አጋር መሆኗን የሚጠቁም ይፋዊ ጉብኝት ከመኆኑም ባሻገር በግላቸም ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ኩራት ነው ሲል ቢቢሲ ዘግቧል ፡፡ ትራምፕ ከንጉስ ቻርለስ ሶስተኛ እና ከዌልስ ልዕልት ጋርም ሲገናኙ ብሄራዊ ክብር ባለው መልኩ ነው ተብሏል ፡፡
ፕሬዚዳንቱ ከባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ጋር በማሪን ዋን ሄሊኮፕተር ሲደርሱ ክብረ በዓል በመሰለ መልኩ በግዙፉ ቅጥር ግቢ አቀባበል ሲደርግላቸው ትርጉሙ ከእንግድነት ባሻገር ነው የሚሉ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ንጉስ ቻርለስ ሳልሳዊ እና ንግስት ካሚላ ዊንደሰር ካስትል ቀድመው ተገኝተዋል ፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ ቆይታ የነበራቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ እና የዶናልድ ትራምፕ የመካከለኛው ምስራቅ ልዩ መልዕክተኛ ስቲቭ ዊትኮፍ ከትራምፕ ቀድመው ዊንድሰር ካስትል መገኘታቸውም ታውቋል ፡፡
የአሜሪካው ምስጢራዊ አገልግሎት እና የእንግሊዙ የሥለላ ተቋም ኤም አይ -6 በርካታ ስራዎችን በመስራት ደህንነቱ የተጠበቀ ከባቢን ፈጥረዋል፡፡ በአራት ሄሊኮፕተሮች ታጅበው ዊንድሰር ካስትል የደረሱት ትራምፕ እና ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በሰረገላ ሲጓዙም አስደናቂ ትዕይንት ፈጥሯል፡፡
ለፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከደማቁ አቀባበል ባሻገር ቁልፍ የዲፕሎማሲ ስራ እንደሚሆንላቸውም ታውቋል፡፡
ዘገባው የስካይ ኒውስና ቢቢሲ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












