ንፅህናው በሚገባ የተጠበቀ ጤናማነቱ በምርመራ የተረጋገጠ የእርድ አገልግሎት እንዲሰጥና የስጋ ውጤቶችን አደራጅቶ ለሃገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አታክልቲ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል ።
ድርጅቱ ለእርድ አገልግሎትና ለተረፈ ምርት ዝግጅት ከፍተኛ ጥንቃቄ እያደረገ እንደሚገኝ በመግለፅ 30 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን አንስተዋል።
የኢዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የከተማ ግብርና ኮሚሽን እንዲሁም ከመዲናይቱ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት ትኩረት በመስጠት ህገወጥ እርድን ለመከላከል ክትትል እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።
ለዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን መሰራቱንም አንስተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ም/ኮሚሽነር ዶ/ር ፀጋዬ ለማ በከተማው ባሉ 3ቱም የቄራ ድርጅቶች የማረጃ ክፍሎችና የእርድ መፈጸሚያ መሳሪያዎችበሀኪም የተመረመሩ ጤናማ ስጋ ለተቋማቱ የሚያሰራጩ የስጋ ማመጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን ጨምሮ ንጽህናቸውና ደህንነታቸውን የማየትና ለስራ ዝግጁ መሆናቸውን የማረጋገጥ ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
በህገወጥ መንገድ የታረደ ስጋ ምርት ለህብረተሰቡ ሲያቀርቡ የነበሩ 350 የስጋ መሸጫ ተቋማት ላይ የማሸግ ስራ መሰራቱን በመጥቀስ ከህገወጥ ቅጣት 5104000 ብር መሰብሰቡን አስረድተዋል።
በ_አማኑኤል ምትኩ












