በሀገሪቱ በየዘርፉ የተመዘገበው ለውጥ ኢትዮጵያ በቀጣይ የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለፁ።
ጳጉሜን 3 የእመርታ ቀን በሳይንስ ሙዚየም “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ ” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡ ቀኑ በሀገሪቱ ባለፉት ሰባት አመታት የተመዘገቡ ሁለንተናዊ ስኬቶች እና ድሎች የሚቃኙበት ነው።
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እንደገለፁት፤ ባለፉት ሰባት አመታት ተግባራዊ የሆኑ የለውጥ ስራዎች አስተማማኝና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት አስችለዋል፡፡ በዚህም ቁልፍ የልማት ዘርፎች በሆኑት በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በገቢ አሰባሰብና በሌሎች ዘርፎች ተጨባጭ እድገት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡
እየተመዘገቡ ያሉ ለውጦች ኢትዮጵያ በቀጣይ ጥቂት አመታት የምትደርስበትን ከፍታ የሚያመላክቱ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የማእድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ እና የተለያዩ ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡













