Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

September 5, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

ሰላምን ማጽናት የጸጥታ ተቋማት ዋነኛ ተልዕኳቸው ነው። የኢፌዴሪ የጸጥታ ተቋማት ዋነኛው ተልዕኮ ሰላምን በመላ ሀገሪቱ ማጽናት ነው፡፡

ይሄን በተመለከተ ከጸጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር ሲደረግ የነበረው ውይይት ዛሬ ተጠቃልሏል፡፡

የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ሰላምና ጸጥታ አስቻይ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን ዋነኛው ግብዐትም ነው፡፡ ይሄን ለማስከበር ሕዝባችን በባህሉና በዕሴቱ ላይ ተመሥርቶ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ፣ የጸጥታ ተቋማት ሚና የማይተካ ነው፡፡

የአሻጥር፣ የከተማና የገጠር ውንብድና፣ የኮንትሮባንድ፣ የሙስና፣ ሕገ ወጥ የሰዎችና የገንዘብ ዝውውር እና የመሳሰሉ ወንጀሎችን በመከላከልና በመቆጣጠር የሕዝቡን ሰላም ማስከበር እንደሚገባ በውይይቱ ላይ በስፋት ተነሥቷል፡፡

የሰዎችና የሸቀጦች ዝውውር ለብልጽግናችን ወሳኝ ናቸው፡፡ ስለዚህም በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ዝርፊያዎችን፣ እገታዎችን እና መሰናክሎችን በተጠና መንገድ መቆጣጠር ይገባናል፡፡ የጸጥታ ኃይላችን ሕዝቡን በየደረጃው በማስተባበር እነዚህን አካላት ከእኩይ ተግባራቸው መግታት፣ ብሎም ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባ አጽንዖት ተሰጥቶበታል፡፡

ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን፣ የማዕድን ቦታዎችን፣ ኢንዱስትሪዎችን፣ የመኖሪያ አካባቢዎችን እና የሕዝብ መገልገያዎችን ደኅንነት ለመጠበቅና አገልግሎታቸው ያለ እንከን እንዲፈጽሙ ለማስቻል የጸጥታ አካላትና የየአካባቢው ማኅበረሰብ ትብብር ወሳኝ መሆኑን በውይይቱ ወቅት ተነሥቷል፡፡ ሕዝቡ ሰላሙን በራሱ እጅ የማስከበር ፍላጎቱ፣ ዝግጁነቱና ዐቅሙ በየጊዜው እያደገ መምጣቱ ተገምግሟል፡፡

ባህላዊና መንፈሳዊ ዕሴቶቹን በመጠቀም የታጠቁ አካላት ወደ ሰላማዊ መንገድ እንዲመጡ እያደረገ ነው፡፡ ከጸጥታ አካላት ጋር ተባብሮ የአካባቢውን ሰላም እያስከበረ ነው፡፡ የጸጥታ አካላት ለሚያከናውኑት ሥምሪትም የመረጃና የሎጂስቲክስ ድጋፍ እየሰጠ ነው፡፡ ይሄን የሕዝቡን ዐቅም ይበልጥ በሥልጠና በማጎልበት ለዘላቂ ሰላም መጠቀም እንደሚገባ በውይይቱ ማጠቃለያ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ለማደናቀፍ በማሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ በኩል የሽብር ተግባር የሚፈጽሙትን ትኩረት ሰጥቶ መከታተል እንደሚገባ በውይይቱ ወቅት የተነሣ ሲሆን፣ በሳይበር ቴክኖሎጂ በኩል መከናወን የሚገባቸው የመከታተልና የመቆጣጠር ሥራዎች ይበልጥ መጠናከር እንደሚገባቸው በውይይቱ ተመልክቷል፡፡

በአንድ በኩል የቴክኖሎጂ የመከላከያና መቆጣጠሪያ ሥራዎችን ለመሥራት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሽብር ፈጣሪዎቹን ለሕግ ለማቅረብ የጸጥታ አካላት በጽኑ መሥራት እንዳለባቸው መመሪያ ተሰጥቷል፡፡ የጸጥታ ተቋማት ወትሮ ዝግጁነት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች ለማስከበር በሚያስችል ደረጃ ላይ መድረሱን በውይይቱ ተገምግሟል፡፡

ኢትዮጵያ ከዘመን ጋር የዘመኑ እና በሕገ መንግሥታዊ ዕሴቶች ላይ የተገነቡ የጸጥታ ተቋማት እየገነባች መሆኗ ተረጋግጧል፡፡ ይሄንን ግንባታ የዘወትር ተግባር በማድረግ መቼም፣ የትም፣ ለምንም ዓይነት ሁኔታ ዝግጁ የሆኑ የጸጥታ ተቋማትን እየገነባን እንድንሄድ የሚያስችል አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡

የኢትዮጵያ ጂኦ ፖለቲካዊ ኩስመና ባከተመበትና ቁመናዋ እየተስተካለ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ የጸጥታ ተቋሞቻችን የሀገሪቱን ሉዓላዊነት፣ ነጻነት፣ ዳር ድንበር፣ ሰላምና ደኅንነት፣ ብሎም የብልጽግና ጉዞ ለማስከበር በሚችሉበት ዐቅም እና ዐቋም ላይ እንደሚገኙ ተረጋግጧል፡፡

ይሄንኑ ወትሮ ዝግጁነት ይበልጥ በማጠናከር፣ የውስጥና የውጭ ችግር ፈጣሪዎችን አደብ አስገዝቶ፣ ሰላምን በሚያጸና ልክ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡ የጸጥታ ተቋማት ዋና ተልዕኮ ሰላምን ማጽናት ነውና፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ነሐሴ 30 ቀን 2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

ማባሪያ ያጣው የጋዛ ጦርነት

Next Post

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዳግማዊ አድዋ ነው-የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዳይሬክተር

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
50
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዳግማዊ አድዋ ነው-የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዳይሬክተር

ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዳግማዊ አድዋ ነው-የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዳይሬክተር

የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ዝግጅት ተደርጓል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ ዝግጅት ተደርጓል-የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት

“የጸጥታ ተቋማት ዋና ተልዕኮ ሰላምን ማጸናት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

"የጸጥታ ተቋማት ዋና ተልዕኮ ሰላምን ማጸናት ነው" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?