እስራኤል ሶሪያ ላይ አዲስ ጥቃት መክፈቷ ተገለፀ።
ከአንድ ቀን በፊት በእስራኤልና ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ስድስት ወታድሮች ህይወት የተቀጠፈበት ቦት ላይ ነው ዘመቻው የተደረገው። ተከታታይ ጥቃት በቀድሞው ወታደራዊ መሰረተ ልማትና ህንፃ ላይ በደቡብ ምዕራብ ደማስቆ “ኪስዋ” የደረሰ ሲሆን፣ እስራኤል ድንበር ተሻጋሪ ዘመቻ ላይ ማተኮሯን ይጠቁማል የሚል መረጃም ተጋርቷል።
የእስራኤል አውሮፕላን አካባቢውን ሲያወድም እንደነበርም አልጀዚራ አረጋግጫለሁ ብሏል። የእስራኤ ጦር በአራት ሄሊኮፕተሮች አካባቢውን ለማረፊያ ለማዘጋጀት ዘመቻ ከፍቷልም ተብሏል። እስራኤል በርካታ ወታደሮቿን በስፍራው በማሰማራት በውል ያልታወቀ የፍለጋ መሳሪያ በማስገባት ቦታው ላይ ለ2:00 ሰዓታት ያህል ቆይታለች።
በእስራኤል እና ሶሪያ ሀይሎች መካከል ግን ምንም ዓይነት ግጭት አልተስተዋለም።
አልጀዚራ እንዳስነበበው
በ-ቢኒያም ካሴ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












