በአሜሪካን ሚኒያፖሊስ በሚገኝ የካቶሊክ ትምህርት ቤት በተከፈተ የተኩስ ጥቃት ሁለት ህፃናት ሲገደሉ 17 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው ተሰምቷል።
በሚኒያፖሊስ የካቶሊክ የህፃናት መማሪያ ትምህርት ቤት ሆን ተብሎ በተከፈተው በዚህ ተኩስ ከቆሰሉት ውስጥ 14ቱ ህፃናት ናቸው። ህፃናቱ በደረሰባቸው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ውስጥ ናቸውም ተብሏል።
በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ህፃናት የ8 እና የ10 ዓመት ታዳጊ እንደነበሩ ተገልጿል። ተኩሱን ከከፈቱት አንደኛው ሮቢን የተሰኘ የ23 ዓመት ወጣት ሲሆን ከዚህ ቀደም ምንም አይነት የወንጀል ሪከርድ እንደሌለበት ተረጋግጧል።
ጥቃቱን ከፈፀመ ኋላ እራሱ ላይ እርምጃ በመውሰድ ብቻውን የተፈፀመ ጥቃት እንዲመስል አድርጓልም ብሏል ፖሊስ፤ ጥቃቱ በተፈፀመት በዚህ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ከ5 እስከ 14 አመት የእድሜ ክልል የሚገኙ ህፃናት የሚማሩበት ነው፤
ወጣቱ ጥቃቱን የፈፀመት ምክንያት ፖሊስ እስካሁን አለመረጋገጡን አስታውቆ፣ ሆን ተብሎ ስለመደረጉ ግን ገልጿል። በአሜሪካ በየዓመቱ መሰል በህፃናትና በሌሎችም ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች በርካታ ስለመሆናቸው ቁጥራዊ መረጃዎች ያሳያሉ።
ዘገባው የሮይተርስ ነው
በ-የአብስራ ሚሊዮን












