በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሀን ከተማ፤ የቀድሞ ታጣቂዎች የተሀድሶ ስልጠና የመክፈቻ መርሀግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሀግብሩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ዴኤታ ተስፋዬ ጎበዛይ ባደረጉት ንግግር፤ ወደ ሰላም ያልመጡ ታጣቂዎችን ወደ ሰላም ለመመለስ መንግስት ከግማሽ በላይ ርቀት ለመጓዝ ዝግጁ ነው ብለዋል።
መንግስት ሰላምን ለማጽናት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ ትጥቅ ፈተው የሚመጡ አካላትን ለመደገፍና ለማቋቋም እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን መንግስት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
የሀገር ሰላም ግንባታ የሁሉንም ዜጋ ርብርብ የሚፈልግ ነው ያሉት ሚኒስቴር ዴኤታው አሁንም ሰላምን ለማጽናን ሰላምን መቀበል ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል። ሰላምን ከመገንባት ጎን ለጎን የልማት ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ላይ መተባበር ይገባናል ሲሉም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ዴኤታ ተስፋዬ ጎበዛይ ጥሪ አቅርበዋል።
በ-ሰላማዊት ወንድወሰን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












