የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የቻይና 80ኛ አመት የድል ቀን በአልን ለማክበር ወደ ቤጂንግ ሊያቀኑ ነው ተብሏል።
ኪም ጆንግ ኡን በመጪው ሳምንት ቻይና የምታከብረውን የሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ 80ኛ አመት በአልን ተከትሎ ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር ወደ ቤጂንግ እንደሚያቀኑ ተገልጻል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እምብዛም የውጪ ሀገራት ጉዞን የማያደርጉ ሲሆን በፈረንጆቹ 2011 ወደ ስልጣን ከመጡ አንስቶ 10 ብቻ የውጪ ሀገራት ጉዞ ስለማድረጋቸው ይነገራል፤ ከነዚህ ውስጥ ቻይና ተደጋጋሚ መዳረሻቸው እንደሆነች የሚነገር ሲሆን የአሁኑ ጉዟቸው ለአምስት ጊዜ መሆኑም ተነግሯል።
ቤጂንግ የአክሲስ ፓወር የተሸነፈበትንና የሁለተኛው የአለም ጦርነት ማብቂያ በከፍተኛ ወታደራዊ ትርኢት ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች። በመጪው መስከረም 3 በሚከበረው በዚህ ከፍተኛ ወታደራዊ ክብረ በአል ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ይገኛሉም ተብሏል።
ዘገባው የአር ቲ ነው።
በ-የአብስራ ሚሊዮን












