የወልቭሱ አጥቂ ስትራድ ላርሰን በዝውውር ገበያው ከኒውካስትል ጋር ስሙ በተደጋጋሚ በመነሳት ላይ ይገኛል።
የፊት መስመር ተጫዋች በአንገብጋቢነት እየፈለገ የሚገኘው ኒውካስትል ዩናይትድ ስትራድ ላርሰን ለመግዛት ሁለት ጊዜያት ያህል ከፍተኛ ሂሳብ ቢያቀርብም ወልቭስ ውድቅ አድርጎታል። ኒውካስትል በሁለተኛ የተሻሻለ 55 ሚሊዮን ፓውንድ ቢያቀርብም ወልቭስ በምንም አይነት ሂሳብ ተጫዋቹን በዚህ ሰዓት መልቀቅ እንደማይፈልግ አስታውቋል።
ስትራድ ላርሰን አሁን ላይ ለክለቡ የልቀቁኝ ጥያቄ እንዳቀረበ እየተዘገበ ሲሆን፤ ተጫዋቹ እንደ አሌክሳንደር ኢሳቅ እና ዮአን ዊሳ ወደ አመጽ ሊያመራ እንደሚችል ተነግሯል። የወልቭስ ሊቀመንበር ጄፍ ሺ ተተኪ ተጫዋች ለማግነት አስቸጋሪ በመሆኑ፤ ዝውውር በአሁኑ ሰዓት ሊከናወን እንደማይችል መግለጻቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












