ሃይደር ሸረፋ በመቀሌ ሰባ እንደርታ እና አዳማ ከነማ በጥብቅ እየተፈለገ ነው ተባለ።
የወቅቱ የፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮን ኢትዮጵያ መድን ተጫዋች የሆነው ሃይደር ሸረፋ በዝውውር መስኮቱ በመቀሌ ሰባ እንደርታ እና አዳማ በጥብቅ እየተፈለገ ይገኛል።
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊጉ ምርጥ ተጫዋች የተባለው ሃይደር፤ በመድን የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ በክለቦ ለተጨማሪ አመት የመቆየት ፍላጎቱ ሳይሳካ መቅረቱን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል።
የተጫዋቹን ግልጋሎት በመፈለግ አሁን ላይ ስማቸው እየተነሳ የሚገኘው የቀድሞ ክለቡ ሰባ እንደርታ እና አዳማ ከነማ ናቸው። ሃይደር ሸረፋ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ በልምምድ ላይ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ ሲሆን፤ ከዚያ መልስ ከሁለቱ ቡድኖች ለአንዳቸው ፊርማውን ያኖራል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












