ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል ያለውን የሰላም ድርድር ለመገምገም የሁለት ሳምንታት ጊዜ ሰጡ።
ፕሬዚዳንቱ የሩሲያውንና የዩክሬኑን ፕሬዚዳንት ካገኙ በኋላ ሰላም በቀጠናው ላይ ይወርዳል የሚል ተስፋ ተጥሎ ነበር። ሩሲያ በዩክሬን ላይ ከባድ ጥቃት አድርሳለች መባሉ ደግሞ ውጥረቱን ሌላ መልክ እንዲይዝ ያደርጋል የሚል ስጋትም በአውሮፓ ህብረት በኩል ይፋ እየሆነ ነው።
በሁለት ሳምንታት ውስጥ በአንድም በሌላም መንገድ የድርድሩ ጉዳይ ያለበትን ሁኔታ እንረዳለን ያሉት ትራምፕ፣ መሬት ላይ የሚኖረው ሃቅም ሌላ መንገድን እንድንከተል እድሉን ይፈጠራል በሚል አሳስበዋል።
አሁን ባለው ሁኔታ ግን ለችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ የሚሰጥ ሀይል በሁለቱም ወገኖች በኩል እንደሌለ ከሚሰጡት መግለጫ አንጻር ለመረዳት አያዳግትም። ትራምፕ ስለሚወስዱት እርምጃ ዝርዝር ማብራሪያ ባይሰጡም ፑቲንና ዘለንስኪ ፖለቲካዊ መግባባት ላይ ካልደረሱ የዋሽንግተን አቋም ከባድ እንደሚሆን ግን ፍንጭ ሰተዋል።
አሜሪካ ከድርድር ሂደቱ የምትወጣበትን አሉታዊ አጋጣሚም ይፈጥራል። የአውሮፓ መሪዎችም ሩሲያ ላይ ብርቱ እርምጃ መወሰድ አለበት በሚል የሙጥኝ ማለታቸው የሞስኮ ጥቃት በኪዬቭ ላይ እንዳይቆም አድርጓል ተብሏል።
ዘገባው የኪዬቭ ፓስት ነው።
በ-ቢኒያም ካሴ












