በጋዛው ጦርነት ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች መካከል 83 በመቶው ንጹሃን መሆናቸውን ከእስራኤል አፈትልኮ የወጣ መረጃ አመላከተ።
በዘመናዊ የጦርነት ታሪክ ውስጥ ይህ ከፍተኛው የንጹሃን እልቂት መሆኑንም ሾልኮ የወጣው የእስራኤል ኢንተለጀንስ መረጃ ጠቁሙል። ዘጋርዲያን እና +972 መጽሄት በጋራ ይፋ ያደረጉት መረጃም ይህኑ የሚያረጋግጥ ነው።

በተለይም +972 መጽሄት በእስራኤል እና ፍልስጤም ጋዜጠኞች በፈረንጆቹ 2010 የተቋቋመ ሲሆን ከቦታው ጥልቅ መረጃዎችንና ትንተናዎችን በመስጠት ይታወቃል። የተመሰረተበት ዓላማም መሬት ላይ ያለውን ሀቅ ማጋለጥ ነው።
በ19 ወራት ውስጥ እስከ ግንቦት 2017 ድረስ እንኳን የእስራኤል ጦር 8,900 ተፋላሚዎችን ከሃማስ እና ከእስላሚክ ጂሃድ (PIJ) ሳይገድል እንዳልቀረ ይፋ ያደረገው መረጃም ይህኑ መረጃ የሚያጠናክር እንደሆነ ተጠቁምዋል።
አብዛኛው ንጹሃን መሆኑን የሚጠቁም አሃዝ ከመሆኑም ባሻገር ከ62 ሺህ በላይ ሰዎች የማለቃቸውን ምስጢርም በተመሳሳይ የሚያጋልጥ ነው። እስከ ግንቦት እንኳን ቢያንስ 53,000 ሰዎች ጋዛ ውስጥ ህይወታቸውን በእስራኤል ጦር አማካኝነት አጥተው ነበር።
ይህም 17 በመቶ ተዋጊዎች ህይወታቸውን አጥተዋል። 83 በመቶዎቹ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ንጹሃን ናችው ወደሚል ድምዳሜ ይወስዳል። የኢንተለጀንሱ መረጃም ይህን ውጤት ያመላከተ ሲሆን ከአሁን በኋላ በጋዛ የሚፈጸመው ጥቃትም ከትላንቱ የከፋ ሊሆን እንደሚችልም ስጋት አለ ተብልዋል ።
አልጀዚራ እንደዘገበው
በ-ቢኒያም ካሴ












