በያዝነው የዝውውር ገበያ ቀኝ መስመር ተከላካዩን ኔልሰን ሴሜዶን ያጣው ወልቭስ፤ ተተኪውን ተጫዋች ከጣሊያኑ ሄላስ ቬሮና አስፈርሟል።
ወልቭስ ተጫዋቹን ለማግኘት 12 ሚሊዮን ፓውንድ ወጪ ያደርገ ሲሆን፤ በክለቡ እስከ 2030 የሚያቆየውን የአምስት አመት ውል አስፈርሞታል። የ23 አመቱ ቻችዋ ከቀኝ መስመር ተከላካይነት በተጨማሪ በአማካኝ ስፍራ መጫወቱ በክለቡ ተመራጭ እንዳደረገው ተመላክቷል።
ቤልጂየማዊው ተጫዋች ባሳለፍነው የውድድር አመት በ36 የሴሪ አ ጨዋታዎች ተሰልፎ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፣ 3 ወደ ግብ የተለወጡ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። በመጀመሪያው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ በሜዳው በማንችስተር ሲቲ የተሸነፈው ወልቭስ ክፍተት ባለበት የሜዳ ክፍል አሁንም ተጨማሪ ዝውውር እንደሚፈጽም ተዘግቧል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












