የአርቲስት ደበበ እሸቱ የአስክሬን ሽኝት መርሐግብር በብሄራዊ ቲያትር እየተካሄደ ነው።
በሽኝት መርሀግብሩ የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀ ስላሴ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ ፣ የባህልና ስፓርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ፣ የአርቲስቱ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የሞያ አጋሮች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።
አርቲስት ደበበ እሸቱ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ቲያትር ጅማሮ ጉልህ አስተዋፅኦ ከነበራቸው ቀደምት አርቲስቶች አንዱ ነበር። ከያኒ ደበበ እሸቱ በማይናወጥ የሀገር ፍቅር እስከመጨረሻው እስትንፉሳቸው ባመኑበት የኖሩና ፅኑ አቋም ባለቤት መሆናቸውም ይነገራል።
ሁለገቡ የኪነጥበብ ባለሞያ ደበበ እሸቱ ከሀገሩ አልፎ በአለም አቀፍ ደረጃ ተሰጥዎን ማሳየት የቻለና የኢትዮጵያን ስም ከፍ ያደረጉ እንደነበሩ የሞያ አጋሮቹ ይመሰክራሉ።
በ-የአብስራ ሚሊዮን
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












