ቻይና ሰው ሰራሽ ማህፀን ያላት ሮቦት እየሰራች እንደሆነ አስታወቀች፡፡ ሮቦቷም ከመውለዷ በፊት ለ10 ወራት ያህል ፅንስ መሸከም እንደሚኖርባት ተገልጿል ፡፡
“ነብሰጡሯ ሮቦት” የሚል ስያሜ የተሰጣት ይህቺ ሮቦት በቻይና ጓንዡ ግዛት ውስጥ የካይዋ ቴክኖሎጂ መስራች በሆኑት በዶ/ር ዣንግ ኪፈንግ ሃሳቡ የቀረበ ሲሆን፣ የመጀመሪያዋ ሮቦትም በሚቀጥለው ዓመት ሙከራ እንደሚደረግላት ተጠቁሟል።
እርግዝና አልሳካ ያላቸው ጥንዶችም አገልግሎቱን ለማግኘት 14,000 ዶላር ያህል እንደሚያስፈልጋቸው ከወዲሁ ተገልጿል፡፡ ይህም ከዚህ በፊት የሰው ሰራሽ ማህፀን ኪራይ በመጠቀም የሚደረገውን የእርግዝና ሂደት ለማካሄድ ይከፈል ከነበረው ከ100,000 እስከ 200,000 ዶላር እጅግ ያነሰ ዋጋ ሆኗል፡፡
በዚህ ዓይነት ቴክኖሎጂ ከሥነምግባር እና ከህግ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ብዙ ጥያቄዎች እና ስጋቶች ይመጣሉ ተብሎ ቢታሰብም፣ የቴክኖሎጂው አምራቾች በዚህ ጉዳይ ከግዛቲቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት እንዳደረጉ ገልጸዋል፤ ነገር ግን ዝርዝር መረጃዎችን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡
በ-ሔርሜላ ተመስገን












