የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት የምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ ሀገራዊ የመጅሊስ ምዝገባ መጠናቀቅን እና የምርጫ ቀን ኩነቶችን አስመልክቶ ጋዜጣሚ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።

ቦርዱ በመላ ሀገሪቱ ሲያካሄድ በቆየው የመራጮች ምዝገባ ከ49 ሺህ በላይ መስጂዶች ምዝገባ መከናወኑን አስታውቋል። በዚህም ከ13 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከነገ ነሐሴ 9–11/2017 ለሚካሄደው የመጅሊስ ምርጫ ለመምረጥ የመራጭነት ምዝገባ ማከናወናቸውን ቦርዱ ገልጿል።
በኦሮሚያ ክልል ከ8 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸው የተመላከተ ሲሆን በዚህም ከፍተኛ የመራጮች ቁጥር የተመዘገበበት ክልል ሆኗል። የትግራይ ክልል በአንዳንድ ምክንያቶች የመራጮች ምዝገባ መዘግየቱን ተከትሎ ላልተወሰነ ጊዜ የመራጮች ምዝገባ እንዲራዘም መደረጉን ነው በመግለጫው የተመላከተው። በመሆኑም በቀጣይ በማሟያ ምርጫ የክልሉ ተወካዮች ምርጫ እንደሚከናወን ነው የተገለፀው።
ከነገ ነሐሴ 9–11/2017 የሚካሄደው ሀገራዊ የመጅሊስ ምርጫ ፍትሐዊና አሳታፊ ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ መቆየቱ የተነሳ ሲሆን በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች ችግሮቹን ከ90 በመቶ በላይ መፍታት መቻሉም ተነግሯል።
በ– አክረም ኑርያ












