የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኢቢሲ) ዲጂታል አሠራርና የይዘት ስብጥር የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ እና ለሌሎች ሚዲያዎች አዲሱን ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ(ዶ/ር) ገለጹ።
ኢቢሲ በራሱ አቅም ያበለጸገውን የሞባይል መተግበሪያ(አፕ) በዛሬው ዕለት በይፋ አስመርቋል።

መረጃ የሰዎችን የዕለት ከዕለት ኑሮ በብዙ መልኩ በሚዳስስበት በዚህ ጊዜ፤ ኢቢሲ መረጃን በተለያዩ አማራጮች የሁሉንም መልክ በሚያሳይ አግባብ ተደራሽ ማድረጉ ለኢትዮጵያ ሚዲያ አዲስ ለውጥ መሆኑንም አስረድተዋል።
ይህን መቀልበስ የሚችሉ፣ የሀገርን መልክ የሚገነቡ፣ ዜጎችን የሚያቀራርቡና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስከብሩ ይዘቶችን ኢቢሲ በዲጂታሉ ዓለም የሚያደርስ አሠራርን ማጎልበቱ ትልቅ እመርታ ነው ብለዋል።
መገናኛ ብዙሃን የሐሰት ትርክትን በመመከት፤ የሀገራችንን የዕድገት አውዶች ማሳየትና ኢትዮጵያዊ ጣዕም ያላቸው ይዘቶች ላይ ማተኮር እንዳለባቸውም ማሳሰባቸውን ተገልጿል።
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












