የብራዚሉ ክለብ ፓልሜራስ በኖቲንግሃም ፎረስት በቂ የመሰለፍ ዕድል የተነፈገውን ግብ ጠባቂ የራሱ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ካርሎስ ሚጌል ፎረስትን የተቀላቀለው ባሳለፍነው የውድድር አመት ከኮረንቲያስ ሲሆን፤ በአሰልጣኝ ኖኖ ስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን የመሰለፍ ዕድል የተሰጠው በአንድ ጨዋታ ብቻ ነው። የፎረስት ተቀዳሚው ግብ ጠባቂ ማት ሴልስ አስደናቂ የውድድር አመት ማሳለፉ፤ በቡድን ስብስቡ በርካታ ግብ ጠባቂዎች ለነበሩት ክለቡ የመሰለፍ ዕድል እንዳይሰጣቸው አድርጓል።
በያዝነው የዝውውር መስኮት ፎረስት ሌላኛው ተጠባባቂ ግብ ጠባቂ ማት ተርነርን ለፈረንሳዩ ሊዮን ሸጧል። ከኖርዊች ሲቲ በነጻ የለቀቀውን አንጉስ ገንን ማስፈረማቸውም ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ የመሰልፍ ዕድሉ የተሟጠጠ የሚመስለው ብራዚላዊው ግብ ጠባቂ ካርሎስ ሚጌል ወደ ሃገሩ ክለብ ይመለሳል ተብሎ ይጠበቃል።
በ-አልፈሪድ ነስሮ
Source:
@NBCEthiopia
Via:
NBCEthiopia












