Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በቲክቶክ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በቲክቶክ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

August 12, 2025
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

NBC Ethiopia

ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም የከተማዋን ሠላም ለማወክ እና በህብረተሰቡ ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እንደማይታገስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ቲክቶክን በመጠቀም ግጭት ቀስቃሽ መረጃ ሲያሰራጩ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ይገኛል ብሏል ፖሊስ፡፡

ፖሊስ በክትትል ከደረሰባቸው መረጃዎች በተጨማሪ የህዝቡን ጥቆማ መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ እና በከተማችን ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር በማሰብ ቲክቶክን በመጠቀም የተለያዩ መልዕክቶችን ሲያሰራጩ የነበሩ ኪሩቤል መላኩ ፣ አህመድ ሻሂር ፣ ምኺኤል አብይ፣ በረከት ዳንኤል እና አብዩ ደግአረገ የተባሉ አምስት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡

ቲክቶክን በመጠቀም ከህብረተሰቡ ስነ ልቦና ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ ከነበሩት እና በአሁኑ ወቅት በፖሊስ ክትትል እየተደረገባቸው ከሚገኙት መካከል አንዱ ብሩክ ተስፋዬ አርአያ የሚባል ግለሰብ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ይህ ግለሰብ ነዋሪነቱ በየካ ክ/ከተማ ሲግናል የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም በህግ የተከለከለን “ካናቢስ” የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ይዞ በመገኘት ወንጀል ክስ ቀርቦበት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 2ኛ አርቲዲ ወንጀል ችሎት ቀርቦ የዋስትና መብት ከተፈቀደለት በኋላ በቀጠሮ ቀን ሳይቀርብ ተሰውሮ በመቆየቱ ፍርድ ቤቱ በሌለበት ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛነቱን በማረጋገጥ በአንድ ዓመት ጽኑ እስራትና በአንድ ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ተከሳሹ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላም ራሱን በመሰወር በማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) የቀጥታ ስርጭት በተደጋጋሚ ጊዜ ከህብረተሠቡ ስነ ልቦና ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን እያስተላለፈ የሚገኝ በመሆኑ ጭምር በፖሊስ እየተፈለገ ይገኛል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያውን በመጠቀም የከተማችንን ሠላም ለማወክ እና በህብረተሰቡ ላይ የደህንነት ስጋት ለመፍጠር በተደራጀ መንገድ በሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች እና ቡድኖች ላይ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር እያደረገ እንደሆነም አስታውቋል፡፡

አዲስ አበባን ከወንጀል የፀዳች እንድትሆንና ዜጎች በሠላም ወጥተው በሠላም እንዲገቡ የአዲስ አበባ ፖሊስ የመዲናዋን ነዋሪዎች ባሳተፈ መልኩ ቴክኖሎጂ መር የሆኑ የወንጀል መከላከልና ምርመራ ስራዎችን በማከናወን በርካታ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑ አስታውሷል፡፡

ዜጎች ሠላምና ደህንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን በተከናወኑ አመርቂ ስራዎችም ባሳለፍነው በጀት ዓመት በከተማዋ የወንጀል ምጣኔን በ43 በመቶ መቀነስ ተችሏል ያለው ፖሊስ፣ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን እጅ ከፍንጅ የመያዝ አቅሙን በማሳደግ እና ዜጎች በቀጥታ ለፖሊስ መረጃ የሚሰጡበትን መንገድ (የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ አፕሊኬሽን ) በማመቻቸት ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝም ነው የገለፀው፡፡

እንደዚህ ዓይነት ድርጊቶች የመዲናችንን ነዋሪዎች ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚከቱና ድርጊቱ በቸልታ ከታለፈም ትልቅ አደጋ ሊያመጣ የሚችል በመሆኑ የድርጊቱን ፈፃሚዎች እንደማይታገስ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፤ መሠል እንቅስቃሴ በሚያደርጉ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ነን ባዮች ላይም ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ፖሊስ አሳስቧል።

Source: @NBCEthiopia
Via: NBCEthiopia
Tags: EthiopiaFacebookMeta
ShareTweetShare
Previous Post

በአዲስ አበባ ከተማ ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ በማዋል 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ማግኘት መቻሉ ተገለፀ

Next Post

ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ በሰራቸው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘገባዎች እውቅና አገኘ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
8
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
15
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
51
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ በሰራቸው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘገባዎች እውቅና አገኘ

ኤን ቢ ሲ ኢትዮጵያ በሰራቸው የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘገባዎች እውቅና አገኘ

ኖቲንግሃም ፎረስቶች የማንቸስተር ሲቲውን ጀምስ ማካቲን ለማስፈረም ተቃርበዋል

ኖቲንግሃም ፎረስቶች የማንቸስተር ሲቲውን ጀምስ ማካቲን ለማስፈረም ተቃርበዋል

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን ጥራትና ደህንነት ለማስጠበቅ የተከናወኑት ተግባራት ስኬታማ ናቸው – አምባሳደር ድሪባ ኩማ

ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ የግብርና ምርቶችን ጥራትና ደህንነት ለማስጠበቅ የተከናወኑት ተግባራት ስኬታማ ናቸው - አምባሳደር ድሪባ ኩማ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?