የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሃማስ ላይ ወታደራዊ ጫና ለማብዛት ተስማምተዋል ተባለ።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤል ጋዛን እጠቀልላለሁ ስትል መደገፋቸውንም ሆነ መቃወማቸውን አላስታወቁም። በሌላ በኩል ኔታንያሁና ትራምፕ በሃማስ ላይ ወታደራዊ እርምጃውን ለማበርታት ተስማምተዋል ሲል አክሲየስ ኒውስን ዋቢ አድርጎ አልጀዚራ ዘግቦታል።
ይህ ደግሞ ቀጠናዊ ውጥረትን ቢያመጣ እንጂ ለሰላም በር አይከፍትም በሚል ትችት እንዲሰነዘርባቸው አድርጓል። ዶናልድ ትራምፕ “ሃማስ በአሁናዊ ሁኔታው ታጋቾችን ፈጽሞ አይለቅም ” ብለዋል።
አሜሪካና እስራኤል ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከባድ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል ቀድሞውን ቢረዱትም አማራጩ ጦርነት እንደሆነ አምነዋል ይላል ዘገባው። መሪዎቹ በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን፤ በተለይም ሪፐብሊካኑ ትራምፕ ‘መልካም የስልክ ውይይት ብለውታል’ ሲሉ መገናኛ ብዙሃን ሲያስነብቡ አድረዋል።
እስራኤል በቀጣይ ስለምታደርገው ነገር ሁሉ መወሰን እንዳለባት ያሳሰቡት ትራምፕ በምንም ሁኔታ ግን ሃማስ በጋዛ ምድር ከእንግዲህ ሊኖር አይችልም በሚል አስጠንቅቀዋል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
በ-ቢኒያም ካሴ












